በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦዲንጋ አቤቱታ አስገቡ


ራይላ ኦዲንጋ
ራይላ ኦዲንጋ

ኬንያ ከሁለት ሣምንት በፊት ያደረገችውን ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉ ያስታወቁት ፕሬዚዳንታዊ ተፎካካሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል።

ሁኔታው ምናልባት ሃገሪቱን ያሰጋትን የፖለቲካ ውጥረትና ግጭት የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል ሮይተርስ ከናይሮቢ ዘግቧል።

ኦዲንጋ ባስገቡት ማመልከቻ በምርጫው ውጤት ላይ የተመዘገበው የድምፅ ሰጭ ቁጥርና የተሰጠው ድምፅ የሚጣጣሙ አለመሆናቸውን፣ ከ27 የምርጫ ክልሎች የደረሱ ድምፆች ህጉ በሚያዝዘው መሠረት አለመቆጠራቸውን፣ እንዲሁም ሌሎችም ችግሮችን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የአሁኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ባለፈው ሣምንት ቢያሳውቅም የኮሚሽኑ አራት አባላት የድምፅ ቆጠራው “ግልፅነት ይጎድለዋል” በሚል ውጤቱን ሳያፀድቁ መቅረታቸው ተዘግቧል።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበርና ዊሊያም ሩቶ መልስ ለመስጠት የአራት ቀናት ግዜ አላቸው።

የተቃዋሚው መሪ ኦዲንጋ ለአምስተኛ ጊዜ በምርጫ ተሣትፈው መሸነፋቸው ነው።

ከዚህ በፊት የተሸነፉት ምርጫዎቹ በመጭበርበራቸው ምክንያት እንደሆነ አስታውቀው የነበረ ሲሆን ያኔ ንትርኮቹ ወደ ረብሻ አምርተው የዛሬ 15 ዓመት በነገረ ሁከት 1 ሺህ 200 ሰው የዛሬ አምስት ዓመት ደግሞ ከ 100 በላይ ተገድለዋል።

XS
SM
MD
LG