በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካዛክስታን ተቃውሞ 164 ሰዎች ሞቱ


ነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት በካዛክስታን በተሳው ተቃውሞ በማዕከላዊ አልማቲ እአአ በጥር 8/2022 የወደመው የባንክ አገልግሎት መስጫ
ነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት በካዛክስታን በተሳው ተቃውሞ በማዕከላዊ አልማቲ እአአ በጥር 8/2022 የወደመው የባንክ አገልግሎት መስጫ

የካዛክስታን ባለሥልጣናት ባለፈው ሳምንት በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተገደሉት 164 ሰዎች መካከል የአራት ዓመት ህጻን ልጅ እንደምትገኝበት አስታወቁ፡፡

ባለሥልጣናቱ 5ሺ800 ሰዎች መታሰራቸውንም ገልጸዋል፡፡

በከፍተኛ ሁኔታ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ለመዋል የካዛክስታን ፕሬዚዳንት ካሲም ጆምራት ቶኪየቭ፣ ጸጥታ አሰከባሪዎች ያለምንም ማስጠንቀቂያ ተቃዋሚዎችን ተኩሰው መግደል የሚችሉ መሆኑን ፈቃድና ትዕዛዝ መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡

የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አባል የሆነቸው ካዛክስታን ፕሬዚዳንት፣ ሩሲያና ፕሬዚዳንት ፑትን የገነፈለውን ተቃውሞ እንዲያረግቡላቸው እርዳታ መጠየቃቸውን ተገልጧል፡፡

በአጸፋውም ሩሲያና የጋራ ደህንነት ስምምነት ያላቸው አባል አገራት፣ እንዲሁም የኢውሮኤሽያን መንግሥታት የወታደራዊ ትብብር ህብረት አገሮች ፣ወታደሮችን ወደ ካዛክስታን መላካቸው ተሰምቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን “ካዛክስታን የራሷን ህግና ሥር ዓት ማስጠበቅ ተቋሞቿንም መከላከል ትችላለች፣ ይሁን እንጂ ያንን ለማድረግ የሰላማዊ ዜጎችን የመቃወም መብት ማክበርና ያቀረቡትን የምጣኔ ሀብትና አንዳን የፖለቲካ ጥያቄዎች መመለስ አለባት” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG