በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጆሃንስበርግ የአክሲዮን ገበያ ከፍ አለ


ፎቶ ፋይል፦ ጆሃንስበርግ፤ ደቡብ አፍሪካ
ፎቶ ፋይል፦ ጆሃንስበርግ፤ ደቡብ አፍሪካ

ቻይና የዜሮ ኮቪድ ፖሊሲዋን ማላላቷን ተከትሎ፣ በደቡብ አፍሪካ የጆሃንስበርግ አክሲዮን ገበያ በማዕድንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱን የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ። ጭማሪው እስከ አሁን ያልታየ ነው ተብሏል።

ቻይና እንደገና ድንበሯን በመክፈቷና የአሜሪካው ፌዴራል ግምጃ ቤትም የወለድ መጠን ጭማሪውን ገታ ያደርገዋል የሚለው ተስፋ የጆሃንስበርግን አክሲዮን ገበያ እንዳነቃቃው ለማወቅ ተችሏል።

የማዕድን ገበያው 2.35 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ጭማሪው የታየው የዜሮ ኮቪድ ፖሊሲዋን በመተዋ የቻይና ኢኮኖሚ እመርታ ያሳያል በሚል ተስፋ እንደሆነ የሮይትረስ ዘገባ አመልክቷል።

ሁለት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አክሲዎንም 3.92 በመቶ እና 3.86 በመቶ ማደጉን ሪፖርቱ በተጨማሪ ጠቁሞ፣ የደቡብ አፍሪካ የመገበያያ ገንዘብ ራንድም በምንዛሪ ረገድ ጥንካሬው እየጨመረ ነው ብሏል።

XS
SM
MD
LG