በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ዕርዳታ ያስፈልገዋል” - የአሜሪካዋ ቀዳማዊ እመቤት


ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን
ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን

በኬንያ የሚገኙ በድርቅ የተጠቁ ሰዎችን ትናንት እሁድ የጎበኙት የአሜሪካዋ ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን፣ ባለጸጋ አገራት በከፍተኛ ድርቅና ቸነፈር ለተጠቃው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ተጨማሪ ልገሳ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የሁለት አፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ትናንት ያጠናቀቁት ጂል ባይደን በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ የ22 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ለጣለው ድርቅና ቸነፈር ትኩረት እንዲደረግ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን ሕይወት ከቀጠፈውና ሰብልን ካጠፋው ድርቅና ቸነፈር የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ አሜሪካ ከፍተኛው ዕርዳታ ለግሳለች፡፡

“እኛ ብቻ መሆን የለብንም፡፡ ሌሎች አገሮችም ሊረዱ የገባል” ብለዋል ጂል ባይደን፡፡

“እንዳለመታደል ሆኖ በዩክሬን ጦርነት አለ፣ በቱርክም የመሬት መናወጥ ተከስቷል፡፡ በመሆኑም የዓለም ትኩረት ተበታትኗል፡፡ እዚህ ግን ሰዎች እየተራቡ ነው” ሲሉ አክለዋል ቀዳማዊ እመቤቷ፡፡

በድርቁ የተጠቁት ቤተሰቦች የሚሉትንም አድምጠዋል ጂል ባይደን፡፡

ቀዳማዊ እመቤቷ በናሚቢያና በኬንያ ያደረጉት ጉብኝት ባለፈው ታህሳስ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተደረገው የዩኤስ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አገራቸው ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደምትጀምር በገቡት ቃል መሠረት የተደረገ ነው ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG