በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የካይሮ ጉዞ በፍልሰተኞች እና በኃይል ምንጭ ጉዳዮች ላይ የተነጣጠረ ነው


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ

የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጦ የሚመጣውን ፍልሰተኛ ለመግታት እና የኃይል ምንጫቸውን ይዞታ በማጠናከሩ ረገድ ሃገራቸው ግብጽን ሁነኛ አጋሯ አድርጋ እንደምታያት የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት እሁድ ተናገሩ።

ግብፅ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ2016 አንስቶ ድንበሯን አቋርጠው የሚፈልሱ ስደተኞችን ያሳፈሩ ጀልባዎች ከሰሜናዊ የባህር ዳርቻዎቿ እንዳይነሱ ብታደርግም፣ በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ የሚያመሩ ዜጎቿ ቁጥር ግን በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።

ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2022 ብቻ 20, 542 ግብፃውያን ጣሊያን ሲገቡ፣ ይህ አሃዝ ከዚያ ሁለት ዓመት በፊት በ2020 ዓም ግን 1,264 ነበር። ይህም አሃዝ በጣሊያን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የታተመ መረጃ እንዳመለከተው ወደዚያች አገር ከፈለሱ ስደተኞች በቁጥር በሃገር ደረጃ ትልቁ ነው።

መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመቅረፍ በያዘችው ጥረት አገራቸው ከግብፅ የሚመጡትን ጨምሮ ህጋዊ ስደተኞችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ወደ ካይሮ ባደረጉት ጉዞ ወቅት ተናግረዋል።

ከግብጹ አቻቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ስደተኞች ጣሊያን ውስጥ ትምህርት እንዲማሩ እና ሥልጠና እንዲከታተሉ የሚያግዝ የገንዝዘብ ድጋፍ የሚሰጥ የሙከራ ፕሮጀክትን አስመልክቶ የተናገሩት ታጃኒ የሰጡት አሃዛዊ መረጃ ግን የለም።

ታጃኒ አክለውም የሊቢያውን ቀውስ ለመፍታት ወደ ምርጫ ለሚያመራ እና አዲስ ህገ መንግሥት እንዲቀረጽ ለሚያዘጋጅ መፍትሔ ጥሪ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG