በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጣሊያን አዲስ የስደተኞች ሕግን በመቃወም ሰልፍ ተደረገ

በሮም፣ ጣሊያን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥት ስደተኞችን በተመለከተ ሊያወጣ እየተዘጋጀ ያለውን ሕግ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።
በሮም፣ ጣሊያን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥት ስደተኞችን በተመለከተ ሊያወጣ እየተዘጋጀ ያለውን ሕግ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በሮም፣ ጣሊያን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥት ስደተኞችን በተመለከተ ሊያወጣ እየተዘጋጀ ያለውን ሕግ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ መሎኒ የሚመራው ወግ አጥባቂ ቀኝ ዘመም መንግሥት ስደተኞች ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበትን መንገድ አስቸጋሪ የሚያደርግ ደንብ አቅርቦ የህግ አውጪው ም/ቤት ሊነጋገርበት መሆኑን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ሊግ ፓርቲ የተሰኘውና የስደተኞችን በአገሪቱ መገኘት የሚቃወመው ፓርቲ፣ ስደተኞች ልዩ ከላለ የሚያገኙበት ደንብ እንዲሻር በመጣር ላይ ነው፡፡ ልዩ ከለላው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባህር አቋርጠው ጣሊያን የገቡ በሺሕ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ከለላ የሚያገኙበት ደንብ ነው፡፡

ደንቡ የስደተኛ ፈቃድ ማግኘት የማይችሉ ሰዎች በአገሪቱ ለሁለት ዓመታት እንዲቆዩ የሚያስችልና፣ ፈቃዱም እንደአስፈላጊነቱ የሚታደስ ነው፡፡ ይህም ሥራ እንዲሰሩና ቤት እንዲከራዩ ያስችላቸዋል፡፡

በሮም በተካሄደው ሰልፍ ላይ በርካታ የሠራተኛ ማኅበራት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ፖለቲከኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG