በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ ቀውሱ በቀጠለባት እስራኤል ምርጫ ተካሂዷል


እስራኤላውያን ዛሬ ብሄራዊ ምርጫ አካሂደዋል፡፡
እስራኤላውያን ዛሬ ብሄራዊ ምርጫ አካሂደዋል፡፡

እስራኤላውያን ዛሬ ብሄራዊ ምርጫ አካሂደዋል፡፡ እአአ ከ2019 ወዲህ ለአምስተኛ ጊዜ በተካሄደው ምርጫ እስራኤላውያን ሀገሪቱን ካሽመደመዳት የፖለቲክ ቀውስ ለመላቀቅ ተስፋ አድርገዋል፡፡

ምንም እንኳ የኑሮ ወድነቱ እየጨመረ፣ የእስራኤል እና የፍስልጤም ውጥረት እየከረረ የኢራን ስጋት ዋና ጉዳይ እየሆነ ቢመጣም በሙስና ክስ ላይ ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ በመሪነት ለማገልገል ብቁ ናቸው ወይ የሚለው ጉዳይ ትልቅ ሥፍራ ይዟል፡፡

የኔታኒያሁ ዋነኛ ተቀናቃኝ የሽግግር ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትና ኔታኒያሁ ከሥልጣን እንዲለቁ አስተዋጽኦ ያደረጉ መካከለኛውን የፖለቲካ መስመር የሚከተሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ ናቸው፡፡

በተከፋፈለው የእስራኤል ፖለቲካ የምክር ቤቱን አብላጫ ወንበር ያሸነፈ አንድ ፓርቲ ኖሮ የማያውቅ ሲሆን መንግሥት ለመመስረት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

የናታኒያሁ ተቃናቃኞች እና የቀድሞ አጋር ፓርቲዎች በሙስና ከተከሰሱት ናታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ ጋር አብረው ለመጣመር ባለመፈለጋቸው 120 ካሉት የምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃቸውን ድምጽ ማግኘት አልቻሉም፡፡

የምርጫው ውጤት ተጠናቆ ከተገለጸ በኋላ መንግሥት ለመመስረት የሚያበቃውን ድምጽ ያገኘ አሸናፊው ፓርቲ መንግሥት ለመመሰረት ወደ ሦስት ወራት እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ አሸናፊ ካልተገኘ ግን ለስድስተኛ ጊዜ ምርጫ መካሄድ እንደሚኖርበት ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG