በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛ ሰርጥን በአየር ደበደበች


የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ በጋዛ የሚታይ ጭስ
የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ በጋዛ የሚታይ ጭስ

እስራኤል፣ ትላንት ሌሊቱን፣ በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብደባዎችን ማካሔዷንና በጥቃቱም፣ ዛሬ ኀሙስ ማለዳ ላይ፣ የጅሃዲስቶቹን የሮኬት ተኳሽ ቡድን መሪን መግደሏን፣ የአገሪቱ ጦር አስታውቋል፡፡

የአየር ድብደባዎቹ የተካሔዱት፣ በዌስት ባንክ የተፈጸመውን የእስራኤል ጥቃት፣ እንዲሁም ከፍልስጥኤማውያን ድንበር ተሻግረው የሚለቀቁ ሮኬቶችን ተከትሎ፣ ለበርካታ ቀናት በቀጠለው ሁከት እና ብጥብጥ ውስጥ መኾኑ ተነግሯል፡፡

የሁለቱም ወገን ባለሥልጣናት፣ ግብጽ፣ የተኩስ አቁም እንዲኖር ለመሸምገል እየሠራች መኾኑን አስታውቀዋል፡፡

ካለፈው ማክሰኞ አንሥቶ በተነሣው ሁከት፣ ሦስት የጅሃዲስቶቹ አዛዦች እና 10 ሰላማውያን ዜጎችን ጨምሮ፣ ቢያንስ 23 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸው ተመልክቷል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ፣ ትላንት ረቡዕ በቴሌቭዥን በአሰሙት ንግግር፣ ከእስራኤል ወገን በአንድም ሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አስታውቀዋል፡፡

በዋሽንግተን የዋይት ሓውስ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቨን፣ ከእስራኤሉ አቻቸው ዛቺ ሃኒቤግ ጋራ፣ ትላንት ረቡዕ የተወያዩ ሲኾን፣ “ውጥረቶችን ማቃለል እና የተጨማሪ ሰው ሕይወት መጥፋትን ስለ መከላከል” አስፈላጊነት፣ በአጽንዖት መናገራቸውን፣ ዋይት ሓውስ በአወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤል ደኅንነቷን ለመጠበቅ እና ራሷን ከሮኬቶች ጥቃት ለመከላከል ያላትን መብት እንደሚደግፍ፣ መግለጫው አክሎ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG