በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ፓርላማ ሊበተን ነው፣ በህዳር ወር ምርጫ ይካሄዳል


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔፍታሊ ቤኔት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዬር ላፒድ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔፍታሊ ቤኔት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዬር ላፒድ

የእስራኤል ፓርላማ እንዲበተን አባላቱ ዛሬ በሰጡት ድምጽ ወስነዋል። በዚህም የአንድ ዓመት እድሜ ያስቆጠረው የጥምር መንግሥት የሚፈርስ ሲሆን በሀገሪቱ በአምስት ዓመት ውስጥ አራተኛዋ የሚሆነውን ምርጫ ማካሄድ ይኖርባታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔፍታሊ ቤኔት ሥልጣናቸውን ለቅቀው ለጥምር መንግሥቱ አጋራቸው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዬር ላፒድ ያስረክባሉ።

ምርጫው እአአ ህዳር 1 ሊካሄድ የታቀደ ሲሆን ከዋና ዋናዎቹ ተፎካካሪዎች መካከል ላፒድ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ይገኙባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ነፍታሊ ቤኔት እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG