እስራኤል የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናዚነትና ጸረ ሴማዊነትን አስመልክቶ በተናገሩት ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ በእስራኤል የሩሲያን አምባሳደር መጥራቷ ተነገረ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ ከአንድ የጣልያን የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ
“የዩክሬን እስካሁን ድረስ የናዚ ርዝራዦች ያሉባት አገር ናት፡፡ ምንም እንኳ አንዳንዶቹና ፕሬዚዳንቱ ራሳቸው አይሁድ ቢሆኑም ሂትለር ራሱ የአይሁድ ዝርያ ነበረው” ብለው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያሪ ላፒድ ንግግሩን “ይቅር የማይባል አሳፋሪና የሚዘገንን ታሪካዊ ጥፋት ነው” ብለውታል፡፡
ዛሬ ሰኞ የተሰጠው የላፒድ ጠንካራ ምላሽ እስራኤል በዩክሬን ጦርነት ላይ ገለልተኝነቷን ጠብቃ ለመቆየት ካላት አቋም የተቃረነ መሆኑን ተገልጿል፡፡