በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ህግ አውጭዎች ከእስራኤል ጋር የሚደረግ ግንኙነትን የሚወነጅል ህግ አወጡ


የሺኣ ሀይማኖት መሪ ሙክታዳ አልሳዳር ኢራቃውያን አደባባይ በመውጣት ውሳኔን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጥሪውን የተቀበሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማዕከላዊ ባግዳድ በመውጣት  የጸረ እስራኤል መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ተገልጿል ባግዳድ፣ ኢራቅ እአአ ግንቦት 26/2022
የሺኣ ሀይማኖት መሪ ሙክታዳ አልሳዳር ኢራቃውያን አደባባይ በመውጣት ውሳኔን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጥሪውን የተቀበሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማዕከላዊ ባግዳድ በመውጣት  የጸረ እስራኤል መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ተገልጿል ባግዳድ፣ ኢራቅ እአአ ግንቦት 26/2022

የኢራቅ ህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት ከእስራኤል ጋር ንግድን ጨምሮ የሚደረግ ማናቸውንም ግንኙነት የሚወነጅል ህግ ትናንት ሀሙስ ማውጣታቸው ተነገረ፡፡ 329 አባላት ካሉት ምክር ቤት በ275 ድምፅ የጸደቀው ህግን ተላልፎ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት የሚያደርግ ማናቸውም ሰው በሞት ወይም በዕድሜ ልክ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ውሳኔን ተከትሎ ተሰሚነት ያላቸው የሺኣ ሀይማኖት መሪ ሙክታዳ አልሳዳር ኢራቃውያን አደባባይ በመውጣት ውሳኔን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጥሪውን የተቀበሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማዕከላዊ ባግዳድ በመውጣት የጸረ እስራኤል መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ተገልጿል፡፡

እስራኤል ከተመሰረተችበት እኤአ 1948 ጊዜ አንስቶ፣ እውቅና ያልሰጠቻት ኢራቅ፣ ከእስራኤል ጋር ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የሌላት በመሆኑ፣ ውሳኔው ተግባራዊ የሚሆንበት መንገድ ግልጽ አለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ እጅግ ያሳሳበት መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ ውሳኔው “ሀሳብን በነጻነት መግለጽን አደጋ ላይ የሚጥልና ጸረ ሴማዊነትን የሚያበረታታ ከመሆኑም ሌላ ይህ ህግ የኢራቅ አጎራባች አገሮች ከእስራኤል ጋር መልካም ግንኙነት ለመመስረትና ለሰዎችም አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር ከገነቡት ድልድይ ጋር የተቃረነ ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG