በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ሦስት ኢራናውያንን በሳይበር ወንጀል ከሰሰች


የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ሦስት ኢራንያውያንን በሳይበር ወንጀል ከሷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ሦስት ኢራንያውያንን በሳይበር ወንጀል ከሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ሦስት ኢራንያውያንን በሳይበር ወንጀል ከሷል። ግለሰቦቹ አሜሪካ እና ሌሎች ሃገራት በሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ተጠቂዎች አውታር ውስጥ ሰብረው በመግባትና በሚጭኑት ፕሮግራም አማካኘት እዛው በመቆየት ተጠቃሚዎችን ከኔት ዎርክ የማስወጣት፣ አገልግሎትን የማቆረጥ፣ እና መሰል ችግሮችን ፈጥረዋል ተብሏል።

ከተጠቂዎቹ መካከል በአሜሪካ የምትገኘው የኒው ጀርሲ ከተማ ጽ/ቤት፣ ሁለት የሂሳብ አያያዝ ድርጅቶች፣ ሁለት የኃይል ኩባንያዎች፣ በዋሽንግተን ግዛት የሚገኝ የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር ቢሮ እና በፔንሲልቬንያ የሚገኝ ከቤት ውስጥ ጥቃት ያመለጡ ዜጎች መጠለያ ይገኙበታል።

በኒው ጀርሲ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጠበቃ የሆኑት ፊሊፕ ሴሊንገር እንዳሉት፣ ተጠርጣሪዎቹ በኮምፒውተር ሥራዓቱ ውስጥ የሚገኙ የተጠቂዎቹን መረጃዎችን በመቆለፍ መልሰው ማግኘት እንዳይችሉ አድርገዋል ተብሏል።

ክሱ ተጠርጣሪዎቹ የኢራንን መንግሥት በመወከል የፈጸሙት ድርጊት መሆኑን ባያመለክትም፣ የአሜሪካ የደህንነት ተቋማት ከኢራን እስላማዊ አብዩታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸችው ወገኖች በመረጃ መርብ በኩል እየጨመረ የመጣ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል። የአሜሪካ ግምጃ ቤት በበኩሉ የሁለቱን ተከሳሾች የቢትኮይን አድራሻ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ማስፈሩን አስታውቋል።

የአሜሪካ የህግ አስከባሪዎች ግለሰቦቹ በመፈለግ ላይ መሆናቸውንና ኢራን ውስጥ ሳይገኙ አይቀርም የሚል ዕምነት እንዳላቸው ተናረዋል።

ሦስቱ ግለሰቦች ያሉበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG