በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራቱ አሜሪካውያን ካልተፈቱ የኢራኑ ድርድር ላይሳካ ይችላል


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስን ልኡክ የሚመሩት ሮበርት ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስን ልኡክ የሚመሩት ሮበርት ማሊ

ከኢራን ጋር እየተደረገው ያለውን የኒዪክለየር ሥምምነቱን የሚመሩት የዩናይትድስ ስቴትስ ባለሥልጣን ቴህራን ያሰረቻቸውን አራት አሜሪካውያን ካልፈታች በስተቀር ዋሽንግተን ድርድሩን መፈጸም እንደሚቸግራት አስታወቁ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስን ልኡክ የሚመሩት ሮበርት ማሊ ኢራን አግታ ይዛቸዋለች የሚሏቸው አራት አሜሪካውያን ከኒዪከለር ሥምምነቱ ጋር የሚገናኙ አይደለም የሚለውን የአሜሪካን ነባር አቋም የደገሙ ቢሆንም ይሁን እንጂ ድርድሩን ለመጀመር እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚቀመጥ መሆኑን ወደ መናገሩ የተቃረቡ መስለዋል፡፡ ሮበርት ስለዚሁ ሲናገሩ

“የተለያዩ ቢሆንም ሁለቱንም ጉዳዮች እንገፋባቸዋለን፡፡ ይሁን እንጂ አራት ሰላማዊ አሜሪካውያን በኢራን ታግተው ባሉበት ሁኔታ የኒዪክሌሩን ስምምነት ብቻ ማሰብ አንችልም፡፡” ብለዋል፡፡

በቅርቡ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ከስለላና ደህንነት ጋር በተያያዘ ነው በሚል በርከታ የውጭ አገር ዜጎችን ይዞ ማሰሩ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG