በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ ወታደሮችና ተጎጂ ቤተሰቦች የኢራን የማዕቀብ ገንዘብ ከመለቀቁ በፊት ባይደንን ካሳ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ በዋሽንግተን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ ላይ የተካሄደውን የአርበኞች ቀን ሥነ ሥርዓት እአአ ኅዳር 11/ 2021
ፎቶ ፋይል፦ በዋሽንግተን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መታሰቢያ ላይ የተካሄደውን የአርበኞች ቀን ሥነ ሥርዓት እአአ ኅዳር 11/ 2021

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኢራንና ኢራን በምትደግፋቸው ኃይሎች ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸውና ጥቃት የደረሱባቸው ከ1ሺ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ ወታደሮችና የቤተሰብ አባላት ለፕሬዚዳንት ባይደን ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ተጎጂዎች አሜሪካውያን ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር በምታደርገው የኒዩክሊየር ስምምነት በማዕቀብ የተያዘውን ገንዘብ ከመልቀቋ በፊት ፕሬዚዳንት ባይደን በቅድሚያ ለተጎጂዎቹ ካሳ እንዲከፍሉ ጠይቀዋል፡፡

ባላፈው ሳምንት ከተጎጂዎች ለፕሬዚዳንቱ የተላከውን ደብዳቤ ቪኦኤ እንደተመለከተው ተጎጂዎቹ ኢራን የኒዩክለር መሳሪያ ሊኖራት አይገባም በሚለው የስምምነቱ ፍሬ ሀሳብ ከባይደን ጋር የሚስማሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ “ለኢራን እንዳይሰጥ በማእቀብ ከታገደው 60 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አንዲት ዶላር እንኳ ከመለቀቋ በፊት አገዛዙ በአሜሪካውያን ተጎጂዎች ላይ ለፈጸመው በደል ካሳ መክፈል ይኖርበታል” ብለዋል፡፡

ባይደን ጥያቄውን ካቀረቡት ተጎጂዎች ጋርም እንዲገናኙ ተጎጂዎቹ ጥያቄቸውን አቅርበዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ በኢራን ከሚደገፉ ሚሊሻዎች ጋር በተደረጉ ውጊያዎች ከ100 በላይ አሜሪካውያን ወታደሮች መሞታቸውን ይናገራሉ፡፡ ኢራን ግን አስተባብላለች፡፡

ይሁን እንጂ እኤአ በ2020 ኢራቅ ውስጥ ዓለም አቀፍ ኃይሎችን በሚያስተናግደው የጦር ሠፈር ላይ ጥቃት በመሰንዘር 100 አሜሪካውያንን ማቁሰሏንና በኢራቅና ሶሪያ የአሜሪካ ኃይሎችን የሚያጠቁ ሚሊሺያዎችን የምትደግፍ መሆኑን አምናለች፡፡

ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ምዕራባውያን ኃያላን አገሮች በአሁኑ ሰዐት ከኢራን ጋር የኒዩክለየር ስምምነቱ ላይ እየተደራደሩ መሆኑን ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG