በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን የሞት ቅጣት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የመብት ተሟጋቾች ተናገሩ


ፎቶ ፋይል፦ በፖሊስ ቁጥጥር እያለች ህይወቷ ስላለፈው ማሻ አሚኒ፣ በመሀል ሮም የተደረገ ሰልፍ 10/29/2022
ፎቶ ፋይል፦ በፖሊስ ቁጥጥር እያለች ህይወቷ ስላለፈው ማሻ አሚኒ፣ በመሀል ሮም የተደረገ ሰልፍ 10/29/2022

ኢራን ባለፈው ዓመት ቢያንስ 582 ሰዎች በሞት መቅጣቷን ሁለት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ትናንት ሀሙስ ባወጡት ሪፖርት አስታወቁ፡፡

ይህ እኤአ ከ2015 ወዲህ በአገሪቱ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

ጽህፈት ቤቱ ኖርዌይ የሆነው የሰብዐዊ መብቶች ተሟጋችና ፓሪስ የሚገኘው “የሞት ቅጣትን በጋራ እንቃወም” የተሰኘው ድርጅት፣ በጋራ ባወጡት ሪፖርት፣ በኢራን የሚፈጸው የሞት ቅጣት ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ በ75 ከመቶ መጨመሩን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሪፖርታቸው “የኢራን መንግሥት ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሞት ቅጣትን ሰዎችን እንደ መጨቆኛና ማስፈራሪያ መሳሪያ እየተጠቀመበት ነው” ብለዋል፡፡

ከተገደሉት ውስጥ ከፊሎቹ በግድያ ወንጀል የተፈረደባቸው ሰዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ባላፈው መስከረም በፖሊስ ቁጥጥር እያለች ህይወቷ ካለፈው ማሻ አሚኒ ሞት ጋር ተያይዞ አራት ተቃዋሚዎች መገደላቸውን የገለጸው ሪፖርቱ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሌሎች ተቃዋሚዎች “የሞት ቅጣት በሚያስፈርድ ወንጀል ለመከሰስ እና ለመገደል አደጋ መጋለጣቸውን” አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG