በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን የአምልኮ ቦታ በተፈፀመ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ

በኢራን በአንድ የሺያ የአምልኮ ቦታ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 15 ሰዎች ሲገድሉ ከ40 በላይ ማቁሰላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በኢራን በአንድ የሺያ የአምልኮ ቦታ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 15 ሰዎች ሲገድሉ ከ40 በላይ ማቁሰላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በኢራን በአንድ የሺያ የአምልኮ ቦታ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 15 ሰዎች ሲገድሉ ከ40 በላይ ማቁሰላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ሽራዝ በተባለችው ከተማ በሚገኘው ሻ ቼራግ መቅደስ ላይ ሲሆን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙሃን ጥቃቱ በአሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ከጥቃት ፈጻሚዎቹ ሁለቱ መያዛቸውን ተናግረዋል።

አይሲስ ጂሃድስኩፕ በተባለው የመገናኛ አውታሩ በኩል ለጥቃቱ ሃላፊነት እንደሚወስድ ሁለት ግዜ አስታውቋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በመቶ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሠልፈኞች ባለፈው መስከረም በፖሊስ እጅ በመሞቷ በኢራን ከፍተኛ ተቃውሞ ባስነሳችው በማሻ አሚኒ መቃብር 40 ቀኗን ለማሰብ በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።

ባለፈው መስከረም የኢራን የሥነ-ምግባር ፖሊስ ከኩርድ ወገን የሆነችውን ማሻ አሚኒን “ሂጃቧን በትክክል አልተከናነበችም” በማለት በቁጥጥር ስር ካዋላት በኋላ በሆስፒታል ህይወቷ አልፏል። ፖሊስ በልብ ድካም መሞቷን ቢናገርም ቤተሰቦቿ ልጃቸው ጤነኛ ነበረች ብለዋል።

በዚህ ሳቢያ በተነሳው ተቃውሞ፣ የሰብዓዊ ድርጅቶች እንደሚሉት፣ ከ200 መቶ በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺሆች እንኳ ባይሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተይዘዋል።

XS
SM
MD
LG