በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢራን የተላኩ ናቸው የተባሉ ሚሳዬሎችን እንግሊዝ ያዘች

ኢራን ሠር የሆኑ ጸረ ታንክ ሚሳዬሎችንና የባሊስቲክ ሚሳዬል ተቀጣዮችን በኦማን ባህረ ሠላጤ ከአንድ ትንሽ ጀልባ ላይ መያዙን የእንግሊዝ ባህር ኃይል አስታውቋል፡፡

የጦር መሣሪያው ወዴት እያመራ እንደነበር የእንግሊዝ ባህር ኃይል አልገለጸም፡፡ “የመረጃ፣ ቅኝትና ሥለላ ድጋፍ” እንደሰጠ የተናገረው የአሜሪካ ጦር ግን ጀልባው የተያዘው በተለምዶ በሕገወጥ መንገድ መሣሪያ ወደ የመን በሚተላለፍበት መሥመር ላይ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ምዕራባውያን ኃይሎች በጀልባ ተጭነው የሚያልፉ በርካታ መሣሪያዎችን በተመሳሳይ መሥመር ላይ በተደጋጋሚ ይዘዋል፡፡ ኢራን በየመን ያሉ ሁቲ አማጽያንን ለመርዳት የምታደርገው ነው ሲሉም ይከሳሉ፡፡ ኢራን ክሱን ታስተባብላለች፡፡

“የመሣሪያዎቹ መያዝ ዓለም አቀፍ ሕግን ለማስከበርና የዓለምን ሰላምና ጸጥታ ለማወክ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ብለዋል የእንግሊዙ መከላከያ ሚኒስትር ቤን ዋላስ፡፡

XS
SM
MD
LG