በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን፣ ሩሲያና ቻይና በጋራ የባህር ላይ ጦር ልምምድ ጀመሩ


ፎቶ ፋይል፦ የባህር ኃይል ወታደሮች የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ምስረታ 70ኛ ዓመት በቤጂንግ ቻይና ሲያከብሩ እአአ ጥቅምት 1/2019
ፎቶ ፋይል፦ የባህር ኃይል ወታደሮች የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ምስረታ 70ኛ ዓመት በቤጂንግ ቻይና ሲያከብሩ እአአ ጥቅምት 1/2019

ኢራን ሩሲያና ቻይና፣ የህንድ ውቅያኖስ የባህር አገልግሎት ደህንነትን ለማጠንከር በሚል፣ በጋራ የሚያደርጉትን የባህር ኃይል ልምምድ፣ ዛሬ ዓርብ መጀመራቸውን፣ የኢራን መንግሥት ቴሌቭዥን አስታወቀ፡፡

ቴሌቪዥን ጣቢያው ዛሬ ባሰራጨው ዘገባው፣ 11 የሚሆኑን የኢራን መርከቦች ዲስትሮየር የተባለውን ጨምሮ ሦስት የሩሲያ የጦር መርከቦችና ሁለት የቻይና ጦር መርከቦች በተሳተፉበት ልምምድ ተከፋይ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብም ከትናንሽ መርከቦችና ሂሊኮፕተሮች በመሆን የልምድዱ ተስታፊ እንደሚሆን የኢራን መግለጫ አመልከቷል፡፡

በሰሜን የህንድ ውቅያኖስ 17ሺ ስኩዌር ኬሎ ሜትር ወይም 10ሺ600 ማይል ይሸፍናል የተባለው ልምምድ፣ የምሽት ውጊያን ፣ የነፍስ አድን ዝጅትና፣ የባህር ላይ ውጊያ ልምምዶችን እንደሚያካትት በመግለጫው ተገልጿል፡፡

ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት በተበላሸበትና የኒዩክለየር ሥምምነት ድርድር ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ከሩሲያና ከቻይና ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠንከር እየሰራች መሆኑንም ዘገባው አመልከቷል፡፡

እኤአ ከ2019 በኋላ ይህ ለሦስተኛው ጊዜ የተደረገ ልምምድ መሆኑን ሲገለጽ፣ ኢራንም ለብቻዋ የምታደርገውን የባህር ላይ ልምምድም እየጨመረች መምጥቷ ተጠቅሷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢራንን የሚጎበኙ የሩሲያና የቻይና የባህር ኃይል ባለሥልጣናትም ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG