በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሆንግ ኮንግ ምርጫ የቻይና ደጋፊዎች አሸነፉ


የምርጫ ጣቢያ፤ ሆንግ ኮንግ
የምርጫ ጣቢያ፤ ሆንግ ኮንግ

በሆንግ ኮንግ ትናንት በተካሄደው የምክር ቤት አባላት ምርጫ የቻይና ደጋፊ የሆኑ እጩዎች በርካታውን ድምጽ አሸንፈው መውሰዳቸው ተሰማ፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው 30 ከመቶ ብቻ መራጮች ተሳትፈውበታል በተባለው በዚህ ምርጫ የቻይና ደጋፊዎች የሆኑት 40 ወንበሮችን ሲያሸንፉ በተለያዩ ሙያና የንግድ ዘርፍ የተሰማሩት ደግሞ 30 መቀመጫዎችን አግኝተዋል፡፡ የተቀረው ጥቂት ውጤት ገና አልተገለጸም፡፡

እኤአ በ2016 ተደርጓል ከተባለው ምርጫ በግማሽ ያህል የቀነሱ መራጮች የተሳተፉበት መሆኑ የተመራጮችን ህጋዊ ተቀባይነት ይቀንሰዋል የሚል ስጋት መፍጠሩም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

“ዘዴሞክራቲክ አላያንስ ፎር ቤተርመንት ኤንድ ፕሮግሬስ” የተባለው ፓርቲ መሪ ስታሪ ሊ ፓርቲያቸው ህጋዊና ህዝባዊ ተቀባይነት አይኖረውም የሚለውን እንደማይቀበሉት መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

ስታሪ ሊ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በዚህ ምርጫ ዝቅተኛ መራጭ መውጣቱ መራጮቹ ከምርጫው ሥርዓት ጋር ችግር ያላቸው መሆኑን የሚያመለክት አይመስለኝም፡፡ ሰዎች ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን እስኪያላምዱ ድረስ በቂ ጊዜ የሚፈልጉ ይመስለኛል” ብለዋል፡፡

በዚህ ምርጫ የሚሳተፉት “አርበኞች” ብቻ ናቸው በሚል በመንግስት የተመረጡ እጩዎች መሳተፋቸው በአንዳንድ አክቲቪስቶችና በውጭ መንግስታት እንዲሁም በሰብአዊ መብት ቡድኖችና የዴሞክራሲ ኃይሎች ሲተች የቆየ መሆኑን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG