በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ ማኒላ ይገኛሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ እና የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ እና የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ

አሜሪካ ከፊሊፒንስ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ የረጅም ዘመን አጋር በሆነቸው አገር ይገኛሉ።

“የደቡብ ቻይና ባህርን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ሕጎችና ደንቦች መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ ከእናንተ ጋር ትቆማለች” ብለዋል ሃሪስ ዛሬ ማኒላ ላይ ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት ሲናገሩ።

ቻይና በፊሊፒንስ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ይዞታዋን በማጠናከር ላይ ነች ይላል የቪኦኤዋ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ከጃካርታ የላከችው ዘገባ።

“በፊሊፒንስ ጦር፣ መርከብ ወይም አውሮፕላን ላይ የሚደረግ ጥቃት በዩናይትድ ስቴትስ የጋራ ምላሽ ይሰጠዋል”” ሲሉ አስጠንቅቀዋል ሃሪስ።

ምክትል ፕሬዚዳቷ እየተናገሩ ያሉት “የማኒላ ፓክት” ስለተሰኘውና፣ እአአ 1951 በዩናይትድ ስቴትስና በአካባቢው አገሮች መካከል የተፈረመውንና በጥቃት ወቅት የጋራ ምላሽ እንዲሰጥ ስለትስማሙበት ሰነድ ነው።

የሃሪስ ጉብኝት፣ በታይዋን ምክንያት በቻይናና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ውጥረት በሰፈነበት ወቅትና የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር ሥልታዊ አጋሮችን በመቅረብ ላይ ባለበት ግዜ እየተደረገ ያለ ጉብኝት ነው።

ከሌሎቹ የኢንዶ ፓሲፊክ አጋሮች አንጻር ፊሊፒንስ ለታይዋን እጅግ ቅርብ መሆኗ ቻይና በታይዋን ላይ ለምትሰነዝረው ማንኛውም ጥቃት መልስ ለመድስጠት አመቺ አገር ነች ተብሏል።

ጉብኝቱ ከፈርዲናንድ ማርቆስ በፊት የነበሩት ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ወደ ቻይና በማድላታቸው ምክንያት ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ላማደስም ነው ተብሏል።

ማኒላ በዱቴርቴ አመራር ወቅት የአደንዛዥ ዕጽ ፖሊሲዋ በአሜሪካ በመነቀፉ፣ ዱቴርቴ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አጸያፊ ስድብ በመስደባቸው ሁለቱ ሃገራት ተኳርፈው ነበር።

XS
SM
MD
LG