በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ቻይናን ወቀሱ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኽሪስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኽሪስ

ቻይና “በደቡብ ቻይና የሚገኙ አብዛኞቹ የባህር ይዞታዎች ይገቡኛል በማለት፣ ማስፈራራትና ማስገደዱን ቀጥላለች” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኽሪስ በዛሬው እለት ተናገሩ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት ሰሞኑን በመጎብኘት ላይ ከሚገኙት ሲንጋፑር ውስጥ ሆነው ነው፡፡

“እነዚህን ማስፈራሪያዎች ለመመከት አሜሪካ ከአጋሮቻችን እና ሸሪኮቻችን ጋር ትቆማለች” ያሉት ኻሪስ “እዚህ ላይ ግልጽ መሆን አለብኝ- በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በኢንዶ-ፓሲፊክ ውስጥ ያለን ተሳትፎ በአንድ የተለየ አገር ላይ ያነጣጠረ አይደለም ፣ ወይም ማንም በአገሮች መካከል አንዱን እንዲመርጥ የቀየሰነው አይደለም። ይልቁንም የእኛ ተሳትፎ፣ በዚህ አካባቢ ላለን አጋርነት እና ተሳትፎ ያለንን ብሩህ አመለካከት ማራመድ ነው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዊብን በሰጡት ምላሽ “አሜሪካ ሆን ብላ ስም ማጥፋት፣ ማፈን፣ ማስገደድና ሌሎች አገሮችን በጉልበት ማስፈራራት ይዛለች ለዚህ ደግሞ ምንም ዋጋ የማትከፍልበትን ሥርዓት እየተከተለች ነው” ብለዋል፡፡

ከማላ ኻሪስ “ በኢንዶ ፓስፊክ ግዛት የሚገኙ አገሮች፣ በየአየር ንብረት ለውጡ ላይ የተደቀነውን አደጋ ይገነዘባሉ፣ የባህሩን ከፍታ መጨመርና የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋው የሚሳየውም ቀውሱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ መሆኑን ያሳያል” ብለዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንትዋ ከሲንጋፕሩ ወደ ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ በዛሬው እለት ማምራታቸውም ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG