በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሄይቲ ፍልሰተኞች


ሄይቲያውያን ፍልሰተኞች
ሄይቲያውያን ፍልሰተኞች

ትናንት እሁድ የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን እና ህግ አስከባሪ መስሪያ ቤት በረራዎች አሳፍሮ ወደሃገራቸው የመለሳቸው ሄይቲያውያን ፍልሰተኞች ስለተባረሩት መንገድ እና በማቆያዎች በነበሩበት ጊዜም ስለነበረው አያያዝ ነቀፋ አሰሙ።

ዕቃችንን እንኳን እንድንይዝ አልፈቀዱልንም፣ ምግብም አልሰጡንም ሲሉ አማርረዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንዲት ቺሊያዊት በማቆያ ካምፖቹ ሄይቲያውያን ከሌሎች ሃገሮች ከፈለሱ ስደተኞች በተለየ መንገድ መያዛቸውን አይቻለሁ ብለዋል።

የባይደን አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስን ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ በሚትገኘው የቴክሳስዋ ዴል ሪዮ ከተማ ድልድይ ስር የተቀመጡትን በሽህዎች የተቆጠሩ ፍልሰተኞች የማስወጣት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ባለፈው ቅዳሜ ነው። ባለሥልጣናቱ ከድንበር ቁጥጥር መስሪያ ቤቱ አቅም በላይ በመሆኑ ነው ብለዋል። የሲዲሲን ትዕዛዝ እያስከበርን ስለሆንን በድንበር በኩል የሚመጡ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፣ ወደመጡበት ሀገራቸው እንመልሳቸዋለን ሲሉ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG