በቅርቡ ከሊቢያ የተነሳውና በሜዲትሬኒያን ባህር ላይ ከመስመትጥ የዳነው የወላለቀ ጀልባ 483 ሰዎችን ጭኖ እንደነበር የግሪክ ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል።
በአደገኛ ማዕበል ውስጥ ሆኖ መቅዘፍ ያልቻለውን ጀልባ የባህር ላይ ድንበር ጠባቂዎች ጎትተው ወደ ዳር ሲያወጡት፣ 25 ሜትር በሚሆነው ጀልባ ላይ 336 ወንዶች፣ 10 ሴቶ እና 128 ሴትና ወንድ ልጆች ተጨናንቀው ተሳፍረውበት እንደነበር ታውቋል።
እንደ አሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ በደቡብ ግሪክ በምትገኘው ክሪት ደሴት አቅራቢያ ሲቀዝፉ የድረሱልን ጥሪ በማስተላለፋቸው ከመስመጥ ሊተርፉ ችለዋል።
የግሪክ የስደተኞች ሚኒስትር የሆኑት ኖቲስ ሚታራቺ ፍልሰተኞቹ ወደ አውሮፓ ኅብረት አገራት እንዲዛወሩ በመጠየቅ ለኮሚሽኑ ማክሰኞ ዕለት ደብዳቤ ጽፈዋል።