በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግሪክ ፍልስተኞችን ያሳፈረች ጀልባ ሰጠመች


ፍልሰተኞች የነፍስ አድን ሰራተኞች ከደረሱላቸው በኋላ እአአ 11/1/2022
ፍልሰተኞች የነፍስ አድን ሰራተኞች ከደረሱላቸው በኋላ እአአ 11/1/2022

የግሪክ ባለሥልጣናት አስቸጋሪ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ ከቱርክ የተነሱ በርካታ ፍልሰተኞችን ይዛ ኢቪያ እና አንድሮስ በተባሉ ደሴቶች መካከል ሌሊቱን የሰጠመችውን ጀልባ ፍለጋና የነፍስ አድን አሰሳ መጀመራቸው ተሰማ፡፡

ግሪክ በኤቪያ ደሴት ደቡብ ምስራቅ ጫፍ በኬፕ ካፈሬስ የባህር ዳርቻ ሁሉም ወንዶች የሆኑ 9 ፍልሰተኞችን ማዳኗን አስታውቃለች፡፡

የባህር የወሰን ጠባቂዎች 68 የሚሆኑ ፍልሰተኞች በሰጠመችው ጀልባ ላይ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

ባላፈው ወር በሌስቦስ እና ኪሪታ ደሴቶች አቅራቢያ በ24 ሰዓት ልዩነት ውስጥ ብዙ ህይወት በቀጠፈው አደጋ በርካታ ፍልሰተኞችን ከከተገለበጡት ሁለት መርከቦች ውስጥ ለማትረፍ ተችሏል፡፡

ከቅርቡ ጊዜ ወዲህ ፍልሰተኞች በቱርክ የየብስ ድንበር አድርገው በግሪክ ደሴቶች በኩል ወደ አገሪቱ ለመግባት የሚያደርጉት ሙክራ መጨመሩን የግሪክ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG