ዋሽንግተን ዲሲ —
ጋና ውስጥ በምዕራብ አገሪቱ ክፍል ከዋና ከተማው አክራ 300 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው አፔይቴ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ 17 ሰዎች ሲሞቱ 59 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የጋና የማስታወቂያ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
የፍንዳታው አደጋ የተነሳው ለማዕድን ማውጫ የሚረዱ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ከሞተር ብስክሌት ጋርና ከሌላ አንድ ተሽከርካሪ ጋር በተፈጠረ ግጭት ነው፡፡
ግጭቱ በተፈጠረበት ስፍራም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ትራንስፎርመር የነበረ መሆኑን ተገልጿል፡፡