በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ቻይና በሃይል ታይዋንን ከመቀላቀል እንድትታቀብ አስጠነቀቁ


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ

ቻይና ሃይልን በመጠቀም ታይዋንን ለመቀላቀል እንዳትሞክር ማስጠንቀቃቸውን የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ለአገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። ኦላፍ ሾልዝ ማስጠንቀቂያውን የተናገሩት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቻንግ ከተመራ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት መሆኑን ገልጸዋል።

“በተናጠል ውሳኔ እና በሃይል፣ በምሥራቅ እና ደቡብ ቻይና ባህር ላይ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት እንቃወማለን” ብለዋል ሾልዝ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር።

“በቻይና በሚታየው የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የሕግ የበላይነት አለመከበር ያሳስበናል” ሲሉ አክለዋል።

ታይዋንን በኃይል ለመቀላቀል የምትዝተው ቻይና፣ በታይዋን አቅራቢያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጨምራለች፡፡

ታይዋን በበኩሏ ጥቃት ቢደርስባት ራሷን እንደምትከላከል ታስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG