በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመኑ ቻንሰለር ስኮልዝ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሴነጋል ጀምረዋል


የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝ
የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝ

የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝ አገራቸው በሴንጋል የጋዝ ፍለጋ ፕሮጀክት ላይ ፍላጎት ያላት መሆኑን ትናንት ዕሁድ በጀመሩት የሦስት ቀን የአፍሪካ ጉብኝታቸው ላይ ተናገሩ፡፡

ጉብኝታቸው የዩክሬኑ ጦርነት በቀጠናው ላይ በሚያስከትለው የፖለቲካ ተጽእኖም ላይ እንደሚያተኩር ተናግሯል፡፡

ጀርመን እና ሌሎቹ የአውሮፓ አገሮች ከሩሲያ በሚያስመጡት የተፈጠሮ ጋዝ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት መቀነስ በሚፈልጉበት በዚህ ጊዜ፣ ሴነጋል ከሞሪታኒያ አዋሳኝ አካባቢ ላይ በቂ የሆነ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ስኮዝ በጉብኝታቸው ወቅት ከሴነጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ "ልውውጡን ጀምረናል በባለሙያዎች ደረጃ የምናደርገውን ጥረትም እንቀጥልበታለን፣ ለውጥና ማሻሻልን ማምጣቱ ፍላጎታችን ነው” ብለዋል፡፡

በሴኔጋል የባህር ዳርቻ የሚደረገው የጋዝ ፍለጋ ፕሮጀክት የሚመራው ቢዮንድ ፔትሮሊየም ወይም ቢፒ የተባለው ድርጅት ሲሆን፣የመጀመሪያው በርሜል ምርት እስከሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደማይደርስ ተነግሯል፡፡

የዛሬ ስድስት ወር ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአፍሪካ የመጀመሪያቸው ጉብኝት የሆነው የጀርመኑ ቻንስለር ከሴነጋል ሌላ ደቡብ አፍሪካን እንደሚገበኙ ተገልጿል፡፡

ሴነጋልና ደቡብ አፍሪካ በመጭው ሰኔ ጀርመን ላይ በሚደረገ የቡድን ሰባት አገሮች ጉባኤ ላይ መጋበዛቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG