በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሣይ የኑሮ ውድነት ያማረራቸው ሠልፍ ወጡ


በዋጋ መናር የተማረሩ በሺህ የሚቆጠሩ ፈረንሣውያን የፓሪስን አውራ ጉዳናዎች ትናንት እሁድ አጨናንቀው ውለዋል
በዋጋ መናር የተማረሩ በሺህ የሚቆጠሩ ፈረንሣውያን የፓሪስን አውራ ጉዳናዎች ትናንት እሁድ አጨናንቀው ውለዋል

በዋጋ መናር የተማረሩ በሺህ የሚቆጠሩ ፈረንሣውያን የፓሪስን አውራ ጉዳናዎች ትናንት እሁድ አጨናንቀው ውለዋል፤ የደመወዝ ጭማሪም ጠይቀዋል።

የዘንድሮው የሥነ-ፅሁፍ የኖቤል ተሸላሚ አኒ ኤርኖ ከግራ ዘመሙ ‘ላ ፍራንስ አስሚዝ’ ፓርቲ መሪ ጃን ሉክ ሚሎሾ ጋር በመሆን ሠልፉን ተቀላቅለዋል።

ሠልፉን የጠሩት የ‘ላ ፍራንስ አስሚዝ’ ፓርቲ መሪ ጃን ሉክ ሚሎሾ መሆናቸው ታውቋል።

“እዚህ ያለሁት ስለተበሳጨሁ ነው። የተበሳጨሁት ደግሞ ሁሉ ነገር በትክክል እየሄደ ባለመሆኑ ነው። የህዝብ አገልግሎቱ መበላሸት፣ በሥራ ላይ የሚደርሠው በደል፣ ትርፍ የሚያጋብሱት ወገኖች ታክስ ያለመክፈላቸው ጉዳይ፣ እነዚህ ጉዳዮች ሁሉ አበሳጭተውኝ ነው” ብለዋል ናታሊ ሜሪያው የተባሉ የሠልፉ ታዳሚ።

“መንግሥት አይሰማንም። ለተወሰኑ ሠዎች ነው የሚያደላው። ይህ መቆም አለበት” ሲሉ አክለዋል።

ሚሎሾ በፓሪስ ለታደመው ሠልፈኛ ባደረጉት ንግግር “የፈረንሣዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን “ደክመዋል” አመራሩም ፈረንሣይን ቀውስ ውስጥ እየዶላት ነው” ካሉ በኋላ፣ ነገ ማክሰኞ በፈረንሣይ አጠቃላይ አድማ እንዲደረግ ጥሪ አድርገዋል።

የትናንቱ ሠልፍ የተጠራው በሀገሪቱ ሸንጎ ከፍተኛ ወቀሳ እያስተናገደና ባለውና ባለፈው ሰኔ በተደረገ ምርጫ የአብላጫ ወንበሩን ባጣው የማክሮን መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሏል።

ለማክሰኞ የተጠራው የትራንስፖርት አድማ ከደሞዝ ጭማሪው አድማ ጋር ሲደመር፣ ወትሮውንም ያለውን ከፍተኛ የጋዝ እጥረት ሊያብብስ ይችላል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG