በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍሮሎሪዳ ግዛት በስደተኞች ፖሊሲ ጉዳይ የባይደን አስተዳደርን ከሰሰ


ፎቶ ፋይል፦ የክፍለ ግዛቲቱ ገዥ ሮን ደሳንትስ
ፎቶ ፋይል፦ የክፍለ ግዛቲቱ ገዥ ሮን ደሳንትስ

በዩናይትድ ስቴትስ የፎሎሪዳ ግዛት የስደተኞች ፖሊሲ ህገወጥ ነው በማለት የባይደን አስተዳደርን ክስ መመስረቱን የፍሎሪዳ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ትናንት ማክሰኞ ይፋ አድርገዋል፡፡

የክፍለ ግዛቲቱ ገዥ ሮን ደሳንትስ የፍሎሪዳ መንግሥት ተቋማት በፍሎሪዳ እንዲሰፍሩ የሚደረጉ ህገወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳይሰጡ ት ዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ህግ አሰካባሪዎችና የፍሎሪዳ አውራ ጎዳናዎች ጠባቂዎች ሰነድ አልባ የሆኑ ስደተኞችን ከደቡብ የድንበር አካባቢዎች ወደ ፎሎሪዳ የሚያጓግዙ አውቶብሶች አውሮፕላኖችንም ሆነ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ክሱን አለማየታቸውን ገልጸው ይሁን እንጂ ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጋር ስለ ስደተኞች ህግ ማሻሻያ ገንቢ የሆነ ውይይት ለማድረግ ፈቃደኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG