በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስፔን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች 35 ፍልሰተኞችን ያዙ

የስፔን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች፣ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ከዕንጨት በተሠራ ጀልባ ሲጓዙ የደረሱባቸውን 35 ፍልሰተኞች፣ ትላንት ጧት፣ ርዳታ ወደሚያገኙበት የግራን ካናሪያ ደሴት አርጊንጊን ወደብ ማድረሳቸው ተነገረ፡፡

ከሰሜናዊ አፍሪካ እና ከሰሃራ በታች ካሉ የአህጉሩ አካባቢዎች የመጡ፣ 32 ሰዎችንና ሦስት ሴቶችን የጫነችው ጀልባ የተገኘችው፣ ከግራን ካናሪያ ደሴት ሁለት ማይል ርቀት ላይ በሚገኘው የማስፖሎማስ ባሕር ዳርቻ እንደኾነ፣ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል፡፡

35ቱም ፍልሰተኞች፣ ከአርጊኒን ወደብ ሲደርሱ፣ በቀይ መስቀል አባላት ርዳታ እንደተደረገላቸው ተነግሯል።

ባለፈው ዓመት፣ 15ሺሕ682 ፍልሰተኞች ወደ ካናሪ ደሴቶች መድረሳቸው ሲነገር፣ ይህም እ.ኤ.አ. በ2021 ከነበረው በ29ነጥብ7 ከመቶ ያነሰ መኾኑ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG