በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን የሚመራው ዕዝ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው” - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ


“የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን የሚመራው ዕዝ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው” - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:24 0:00

“የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን የሚመራው ዕዝ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው” - ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ

በመላው ኢትዮጵያ ተፈጻሚ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ። በአሁኑ ጊዜ በሀገር ህልውና ላይ የተደቀኑትን አደጋዎች በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም አዳጋች ሆኗል በሚል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የአስቸኳይ ዐዋጅ ቁጥር 5/2014 በተወካዮች ምክር ቤት በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ዛሬ ጸድቋል፡፡

ዐዋጁ ከትናንት በስቲያ ጥቅምት 23 ጀምሮ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፣ ዐዋጁን ለማስፈጸም በጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የሚመራ የአስቸኳይ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙም ይታወሳል፡፡

በአዋጁ አስፈላጊነትና በሚወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያ የምክር ቤቱ አባላት ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል አዋጁን ለማስፈጸም የተቋቋመው የአስቸኳይ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ለምን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አይመራም የሚል ይገኝበታል፡፡

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ “የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን የሚመራው ዕዝ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑን አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG