በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅዳሴው ግድብ ሙሊት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይጀመራል


ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የኅዳሴውን ግድብ መሙላት እንደምትጀመር የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ትናንት የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በሆኑት ሲሪል ራማፎዛ ሰብሳቢነት የተካሄደው ውይይትም ሙሊትን የማዘግየት አቅጣጫ የተያዘበት አለመሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የውሃ ሙሊት መጀመር የግድቡ ግንባታ ሂደት የደረሰበት ደረጃ የግድ የሚለው እንጂ ስምምነት ላይ ከመድረስ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑንም ዶ/ር ስለሽ አስረድተዋል።

“ምንም ልታደርገው አትችልም ግድቡ እኮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል ሚኒስትሩ።

ቅድመ ሁኔታ ደግሞ ማንም በሌላ ሉዓላዊ ሃገር ላይ ማስቀመጥ አይችልም በማለትም አክለዋል።

በአፍሪካ ኅብረት በተመራው የትናንትናው የኅዳሴ ግድብ ውይይት ላይ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር ሲሳተፉ የታዩት የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ያደረጉትን የስልክ ቃለ መጠይቅ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኅዳሴው ግድብ ሙሊት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይጀመራል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:32 0:00


XS
SM
MD
LG