በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢና የካሜራ ባለሞያው ከእስር ተለቀቁ


የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢና የካሜራ ባለሞያው ከእስር ተለቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢና የካሜራ ባለሞያው ከእስር ተለቀቁ

ለአራት ወራት በእስር ላይ የነበሩት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ አሚር አማን እና ፍሪላንስ የካሜራ ባለሞያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከእስር መለቀቃቸውን ጠበቃቸው ገለፁ።

የሁለቱ ዘጋቢዎች ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረ መድሕን ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት፤ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እንዲፈቱ ማክሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ዕረቡ መጋቢት 21 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው የይግባኝ አቤቱታ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔው እንዲሻርለት ጠይቆ ነበር።

ሆኖም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ የሚያቀርባቸው ምክኒያቶች ተመሳሳይ መሆናቸውን በመግልፅ መከራከሪያ ማቅረባቸውን አቶ ታደለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የሁለቱን ወገን ክርክር ያደመጠው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትናንት ሐሙስ መጋቢት 22 በሰጠው ውሳኔ የሥር ፍርድ ቤት በዋስትና ጉዳይ ላይ የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።

በዚህም ውሳኔ መሰረትም ለአራት ወራት በእስር ላይ የነበሩት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ አሚር አማን እና ፍሪላንስ የካሜራ ባለሞያ ቶማስ እንግዳ በ60 ሺሕ ብር ዋስ ዛሬ ከምሳ በኋላ ከእስር መለቀቃቸውን ጠበቃቸው ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በሚመለከት ባጠናቀረው ዘገባ ምክንያት "መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውን ቡድን ረድተሃል ተብሎ የተወነጀለው ጋዜጠኛ ጉዳይ በሃገሪቱ የሚዲያ ነጻነት እያሽቆለቆለ መሆኑን አጉልቶ የሚያሳይ ነው" ሲሉ ተሟጋቾች ተናገሩ።

/በአሜሪካ ድምጿ ሳሌም ሰሎሞን የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG