በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ጤና ዳታ - በማሕሌት ቆንጆ ሰለሞን


የኢትዮጵያ ጤና ዳታ - በማሕሌት ቆንጆ ሰለሞን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

የኢትዮጵያ የጤና ዳታ የተሰኘው ድረ-ገጽ በኢትዮጵያ እናው በመላው አፍሪካ ላይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዘው በተለያዩ መግስታዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተዓማኒ ምንጮች ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስበው እንዲገኙ የሚያግዝ እና ከእንግሊዘኛ በተጨማሪም በአማርኛ፣ ትግረኛ፣ ሶማሌኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ ድረ-ገጽ ነው፡፡

በሃያ አንደኛው ከፍለዘመን መረጃ በሃገራትም ሆነ በግለሰቦች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ፣ አኗኗር ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ እንዲሁም ማሕበራዊ እና ጤና ላይ ትልቅ ሚና እንዳለው ቸል የማይባል ሃቅ ነው፡፡

ይሁናና የመረጃዎች ጥራት፣ ጊዜያዊነት፣ ሃቀኝነት እና አቀራረብ በራሱ ለተጠቃሚው ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጤና መረጃም ከሰሞኑ እነዚህን ሁሉ ባማከለ መልኩ 'የኢትዮጵያ የጤና ዳታ' (መረጃ) የተሰኘ ድረ-ገጽ(https://ethiopianhealthdata.org/) ከኮቪድ 19 ጋር ተያየዘው በየቦታው ያሉ መረጃዎችን በአንድ ላይ አሰባስቦ በተለያዩ ቋንቋዎች ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ መላው አፍሪካን ላይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዘው የሚውጡት በተለያዩ ሕጋዊ ድርጀቶች ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስበው እንዲገኙ የሚያገዝ ድረ-ገጽ ነው፡፡

ድረ- ገጹ ከእንግሊዘኛ በተጨማሪም በአማርኛ፣ ትግረኛ፣ ሶማሌኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ቀላል አሃዛዊ መረጃን ከሚፈለጉ ጀምሮ ለጥናት እና ለምርመር እንዲሁም ለፖሊሲ ቀረጻ ሊጠቀሙበት ለሚፈለጉም አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የድረ-ገጹ መስራች ማሕሌት ቆንጂት ሰሎሞንን በአሜሪካን ሃገር በሜሪላንድ የጤና ቢሮ ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ የሕብረተሰብ ሳይንስ እና በጤና መረጃ ላይ ባለሞያ ናት፡፡ ማሕሌት ድረገጹን ከኮቪድ 19 በኋላም በተለያዩ የጤና ዘርፎች እና ጉዳዮች ላይ መረጃ መስጠቱን እንደሚቀጥል ጠቁማለች፡፡



XS
SM
MD
LG