በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ግብርና መጻዒ እጣፈንታ እና የዘረመል ለውጥ ውዝግብ


የኢትዮጵያ ግብርና መጻዒ እጣፈንታ እና የዘረመል ለውጥ ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:30 0:00

ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ተከልከሎ የቆየው በእንስሳት እና በእጽዋት ላይ የሚካሄድ የዘረመል ለውጥ (ቅይስ) አካል GMO ምርምር  ከአስር ዓመት በፊት ተጀምሯል፡፡ ይሁንና ጉዳዩ በባለሙያዎች እንኳን ሳይቀር አከራካሪ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉዳይም ላይ የባለሞያ የሆኑትን በኢትዮጵያ ግብርና ኢኒስቲትዩት የግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ አስተባባሪ ዶ/ር ታደሰ ዳባን እና በፊንላድ ሂልስንኪ ዩኒቨርስቲ የድህረ ዶክትሬት ተመራማሪ የሆኑትን ዶ/ር ክፍለማሪያም የኋላን አነጋግረናል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ተከልከሎ የቆየው በእንስሳት እና በእጽዋት ላይ የሚካሄድ የዘረመል ለውጥ (ቅይስ) አካል GMO ምርምር ከአስር ዓመት በፊት ተጀምሯል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታትም የምርምር ስራ የተካሄደባቸው BT ጥጥ በተገደበ መልኩ ለሙከራ ወጥተው እየተፈተሹ ይገኛሉ፡፡

ይህን ተከተሎ በዘርፉ ባለሙያ የሆኑ ግለሰቦች እና ሁኔታው የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ይልቅ በድህነት ውስጥ የሚኖረውን የኢትዮጵያን ገበሬ ማዳበሪያና የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን ዘሮች ለሚሽጡ ኩባንያዎች አሳልፎ በመስጠት ለባሰ ድህነት ያጋለጠዋል፣ የዘር አቅርቦት እጥረት፣ በዓለም አእቀፍ ገበያ ውስጥ በተፈጥሯዊ ምርቶች(Organic) የመወዳደር አቅሟን ያሳጧታል፣ ለአካባቢ ብክልት ተልቅ ሚና ይጫወታል እንድሁም በጤና ላይ የሚያመጡት ተጽእኖ ተለቅ ነው የሚሉ አክቲቪስቶች ኢትዮጵያ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የግብርና ምርቶች ላይ ገደብ እንድትጥል እንቅስቃሴዎች ጀመረዋል፡፡

በዚህ ጉዳይም ላይ የባለሞያ አስተያየቶቻቸውን ይሰጡ ዘንድ በኢትዮጵያ ግብርና ኢኒስቲትዩት የግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ አስተባባሪ የሆኑትን ዶ/ር ታደሰ ዳባን እና በፊንላድ ሂልስንኪ ዩኒቨርስቲ የድህረ ዶክትሬት ተመራማሪ የሆኑትን ዶ/ር ክፍለማሪያም የኋላን ስለ ምርመሩ የራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
XS
SM
MD
LG