በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሂዩማን ራይትስዎች ዘገባ


“የትግራይ ተወላጆች ተለይተው ይታሰራሉ። የገቡበት የማይታወቅ እና የንግድ ቤታቸው የተዘጋም አሉ።” ይላል ሂዩማን ራይትስዎች በትናንትናው ዕለት ያወጣው ሪፖርት።

ሪፖርቱ አክሎም የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት ካለፈው ሰኔ ወር መገባደጃ አንስቶ አዲስ አበባ ላይ “በዘፈቀደ ታስረዋል” ያላቸውን የትግራይ ተወላጆች “ያሉበትን እንዲያሳውቁ፤ ለተከሰሱባቸው ወንጀሎች ተጨባጭ ማስረጃ ያልተገኘባቸውም እንዲለቀቁ እና ‘አድልኦ’ ያለበት ያለው አያያዝ እንዲያቆም” ሲል ጠይቋል።

የሂዩማን ራይትስዎች ናይሮቢ በሚገኘው የድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት ይፋ ባደረገው ሪፖርት

“በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ለስምንት ወራት ያህል የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ ሰኔ 21, 2013 ዓም የመንግስት ኃይሎች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ የትግራይ ኃይሎች በምትኩ መቀሌን መልሰው ተቆጣጠሩ” ሲል ይንደረደራል።

“ከዚያም ፈጥነው ወደ አጎራባች አፋር እና አማራ ክልሎች በመግፋት መጠነ ሠፊ መፈናቀል አስከተለ።” ይላል። “ከዚያ ጊዜ አንስቶም አዲስ አበባ ላይ በትግራይ ተወላጆች ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የሚፈጸሙ ብርቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጥሰቶች ተባብሰዋል።” ሲል ይከሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የሂዩማን ራይትስዎች ዘገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00


XS
SM
MD
LG