ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለፉት ሦስት ዓመታት በውጭ አገር ከሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በተለየያ መልኩ ወደ አገር ውስጥ የገባው የገንዘብ ድጋፍ መጠን ወደ 9 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ የህዝብ ግንኙነት ድሬክተር አቶ ወንደሰን ግርማ ተናግረዋል፡፡
በኮቪድ-19 እና በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተጎዳውን የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ለመደገፍ ዳያስፖራው ማህበረሰብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚያደርገው ድጋፍ እየጨመረ መምጣቱንም አቶ ወንደሰን ይገልጻሉ፡፡
በዓመት ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ የነበረው በተጠቀሱት ችግሮች በአማካይ ወደ ሶስት ቢሊዮን ዶላር የወረደ ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን ወደ 3.6 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡