የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኅብረተሰቡ አጀንዳ አሰባስቦ በቅርቡ ውይይት እንደሚያስጀምር አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎች በመዘዋወር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መወያየቱን አመልክቷል፡፡
ወደ ትግራይ ክልል መሄድ በሚችልበት ጉዳይ ላይ ከአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ፕሬዚዳንት ኦባሳንጆ ጋር ሲወያይ መቆየቱን ለቪኦኤ ያስታወቀው ኮሚሽኑ፣ በቅርቡ ወደ ትግራይ ክልልም እንደሚሄድ ገልጿል፡፡
ምክክሩ ሁሉንም አካታች ቢሆንም፣ በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙ አካላት፣ ከነትጥቃቸው የምክክሩ አካል መሆን እንደማይችሉ ጠቁሟል፡፡ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን የምክክሩ አካል ማድረግ ስለሚቻልባቸው መንገዶችም ኮሚሽኑ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/