በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሻንጋይ ላይ አይሮፕላን ተቃጠለ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦዪንግ 777 የጭነት አይሮፕላን ቻይና ውስጥ ሻንጋይ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ዛሬ በእሳት ተያይዟል።

ኢቲ - ኤአርኤች በሚል በረራ የተመዘገበው ቦዪንግ 777 የጭነት አይሮፕላኑ ሻንግሃይ ፑዶንግ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ በእሳት እንደተያያዘበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማኅበራዊ ሚድያ ገፆቹ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አይሮፕላኑ በእሳት የተያያዘው ጣቢያው ላይ ዕቃ እየጫነ ሳለ እንደነበረ አየር መንገዱ አመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላይ ጋር ተባብሮ ቃጠሎውን በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንና ከምድር ላይ ሠራተኞቹም ሆነ ከበረራ ቡድኑ አባላይ ጉዳት የደረሰበት ማንም እንደሌለ አየር መንገዱ አስታውቋል።

ተጨማሪ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሻንጋይ ላይ አይሮፕላን ተቃጠለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00XS
SM
MD
LG