በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድን እየተሻገረው ይሆን?


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድን እየተሻገረው ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድን እየተሻገረው ይሆን?

ዩናይትድ ስቴትስ ከጥቅምት 29/2014 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ መንገደኞችን ተቀብላ ለማስተናገድ በማሰብ፣ የበረራ እገዳ ጥላባቸው የነበሩ 33 አገሮችን ጭምር እገዳውን ልታነሳለቸው ባለፈው ወር ውስጥ ወስናለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የጉዞ አገልግሎት ማህበር ሥራ ዋና አስጻፈሚ ሮጀር ዶው፣ “ይህ ከተጓዦች ጋር ለተሳሳሩ የንግድ መስኮች መነቃቃት፣ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስን መጎብኘት ለሚፈልጉ ቱሪስቶች ከፍተኛ እድል ይሰጣል" ብለዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ድሬክተር፣ አቶ ንጉሡ ወርቁም ይህ ትክክል መሆኑን ገልጸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ የዓለም አየር መንገዶች በጠቅላላ፣ አሁን ያሉበት ሁኔታ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን ይናገራሉ፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቀውስ እጅግ ከተጎዱት ዘርፎች አንዱ አየር መንገዶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ በርካቶቹ አየር መንገዶች ስሙ ከአደባባይ፣ አውሮፕላኖቹም ከሰማይ አልጠፉም፡፡ መሪዎቹ በወረርሽኙ እጅግ የተጎዳ መሆኑን ባይደብቁም ፈተናውን በጥንካሬው አልፎ ከዚህ መድረሱን ይናገራሉ፡፡ አቶ ንጉሡ ወርቁ ጋር ያደግነውን ቆይታ ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG