በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የብዙኃን መገናኛ ነፃነት አደጋ ላይ ወድቋል” /ዶ/ር ዳንኤል በቀለ/


“የብዙኃን መገናኛ ነፃነት አደጋ ላይ ወድቋል” /ዶ/ር ዳንኤል በቀለ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00

“የብዙኃን መገናኛ ነፃነት አደጋ ላይ ወድቋል” /ዶ/ር ዳንኤል በቀለ/

ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት፣ የብዙኃን መገናኛ ነፃነት አደጋ ላይ መውደቁን ቀጥሏል፤ ሲሉ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ ዛሬ በዐዲስ አበባ በተከበረው የዓለም የብዙኃን መገናኛ ነፃነት ቀን ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በኢትዮጵያ በብዙኃን መገናኛ ሠራተኞች ላይ እየታየ ያለው እንግልት እና እስር አሳሳቢ ኾኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አቶ አማረ አረጋዊ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት መሠረት እንዲኖረው፣ መንግሥት፣ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል፤ ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የብዙኃን መገናኛ ምኅዳሩን ለማስፋት የሚያግዙ፣ የፖሊሲ እና የዐዋጆች ማሻሻያ ቢደረግም፣ አተገባበራቸው ላይ ግን ክፍተት ታይቶባቸዋል፤ ተብሏል፡፡ አሁን በልዩ ልዩ የብዙኃን መገናኛ ዘዴ ባለሞያዎች ላይ የሚታየው የሰፋ እስር እና ክሥ ጋዜጠኞችን እያሸማቀቀ እንደኾነም፣ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG