በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠራተኞቹ እንደታሰሩ ገለፀ


የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያ መንግሥት የተመድን ሥራ ሲሠሩ ያሰርኩት የለም ብሏል

የተባበሩት መንግሥታት ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ጦርነት ውስጥ ባለባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ፣ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የሚሠሩ 72 አሽከርካሪዎች መታሰራቸውን አስታውቋል፡፡

ይህ መግለጫ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚሠሩት 22 የድርጅቱ ሠራተኞች፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን የእስር ዘመቻ ተከትሎ፣ አዲስ አበባ ውስጥ በፌዴራል መንግሥቱ ታስረዋል ሲል ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል ስድስቱ ተፈተዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል "የሀገሪቱን ሕግ በመተላለፍ እንጂ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ በመሆናቸው እና በድርጅቱ ሥራቸው ምክንያት የታሰሩ የሉም" ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፣ የሀገሪቱን ሕግ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ የታሰሩ ሰዎች ውስጥ የተመድ ሰራተኞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ከተመድ ሥራ ወይም ከማንነት ጋር በተያያዘ የታሰረ ሰው የለም“ ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠራተኞቹ እንደታሰሩ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:04 0:00


XS
SM
MD
LG