በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ገለፁ


ድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00

ድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ገለፁ

በኢትዮጵያ ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የሚያጓጉዙ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሁለት አሽከርካሪዎች እና በጥቃት ባለቤታቸውን ያጡ አንድ እናት፤ ከጅቡቲ በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች በኩል ወደ መሃል የአገሪቱ ክፍሎች የሚሠሩ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ገልፀዋል። ግድያ፣ የአካል ጉዳትና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሁለት ወራት ውስጥ አምስት አሽከርካሪዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሲገደሉ፤ ሦስት ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ገልጿል።

ከአሽከርካሪዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያደረገው የመንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር በበኩሉ የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ተገቢነት አረጋግጦ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG