በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐቃቤ ሕግ በእነዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የመሰረተው የክስ ይዘት


ዐቃቤ ሕግ በእነዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መዝገብ በተዘረዘሩ በ62 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ። ክስ የተመሰረተባቸው "ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ የክልሉን መንግሥት ለመለወጥ እና በአገር መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት በማድረስ የፌዴራል መንግሥት በኃይል ለመቆጣጠር በፈፀሙት ወንጀል ነው" ተብሏል።

ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው፣ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የክልል መንግሥት ካቢኔ አባላት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መግልጫ አስታውቋል። በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በተደረገው ጥቃት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢፈርት ድርጅቶች፣ የግልና የመንግሥት ድርጅት አመራሮች፣ የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመራር አባላት፣ በትግራይ በተካሄደው ኢ-ሕገ መንግስታዊ ምርጫ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሊቃነ-መናብርትና የቀድሞ የህውሀት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ታዋቂ ግለሰቦችም ላይ የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።

ክሱ የተመሰረተው በሁለት የወንጀል አንቀጽ ስር ሲሆን የመጀመሪያው በኃይል፣ በዛቻ፣ በአድማና ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ኢ-ሕገመንግስታዊ ምርጫ በማካሄድ በሕገ-መንግስት የተቋቋመና እውቅና ያለውን የክልሉን መንግስት ለመለወጥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ነው ተብሏል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ዐቃቤ ሕግ በእነዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የመሰረተው የክስ ይዘት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00



XS
SM
MD
LG