በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ተመድ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥን አሁንም በጽኑ የሚያሳስባቸው መሆኑን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በሰብአዊ ቀውሱ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቹን ሁሉ ለመርዳት በኢትዮጵያ መንግሥትና በአገሪቱ ባሉት የተባበሩት መንግሥታት ባልደረቦች መካከል ለሚደረገው የትብብር ጥረት ዋና ጸሃፊውም ትልቅ ክብደት የሚሰጡት መሆኑን ቃል አቀባያቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

ሰብአዊ ችግሮችን ለማቃለልና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ፣ አስቸኳይ እምጃዎች በተከታታይ መወሰድ የሚገባቸው መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ዋና ጸሀፊው፣ በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙት የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የስደተኞቹን ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ፣ የድርጅቱ የጸጥታና ደህንነት ምክትል ዋና ጸሀፊ ጊሊስ ማሾድ እንዲሁም የዓለም ምግብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ድሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ጋር የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው አዎንታዊ ንግግር ዋና ጸሃፊውን ማስደሰቱን የቃል አቀባያቸው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

አስከትሎም መግለጫው ንግግሮቹ የተከናወኑት በትግራይ ክልልም ሆነ በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉና በየስደተኛ መጠለያ ጣቢያው ለሚገኙ ተጎጂ ሰዎች የሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ ገለልተኝነትና ዘላቂ በሆነ መንገድ ያለዕንቅፋት እንዲመቻች ዋና ጸሀፊው ባደረጉት ጥሪ መሠረት መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG