በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚስት መጽሔት ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነርን የሥራ ፈቃድ ነጠቀ


የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለኢኮኖሚስት መጽሔት የኢትዮጵያ ወኪል ቶም ጋርድነርን በጻፈለትና በማኅበራዊ ገጹ ላይ ባጋራው ደብዳቤ፤

“ፈቃዱ የተሰጠህ ሞያው የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር እና የሀገሪቱን ሕግ እና ደንብ በጥብቅ አክብረህ አንድትሠራ ሲሆን እነዚህን የጋዜጠኝነት ሞያ መስፈርቶች አለማክበርህ አሳዝኖናል” ይላል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚስት መጽሔት ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነርን የሥራ ፈቃድ ነጠቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚስት መጽሔት ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነርን የሥራ ፈቃድ ነጠቀ

በዚሁ ደብዳቤ ላይ “ጋዜጠኛውን በተደጋጋሚ አነጋግረነዋል በቃል እና በጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ብንሰጠውም የተሳሳተ አሠራሩን ለማስተካከል ፈቃደኛ ሆኖ አላገኘነውም” ያለው የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣኑ የሥራ ፈቃዱ መሰረዙን አስታውቋል፡፡

“ኢኮኖሚስት መጽሔት በምትኩ ሥራውን አድላዊ ባልሆነ እና በነጻነት የሚሠራ ነጻ ጋዜጠኛ የሚመድብ ከሆነ በደስታ እንቀበላለን” ብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ የጋዜጠኛውን አና የድርጅቱን የኢኮኖሚስትን ምላሽ ለማግነት ጥረት እያደረግን ነው እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን፡፡

XS
SM
MD
LG