በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕገ ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለዉን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሽፋን በማድረግ ህገ ወጥ ድርጊት በሚፈጽሙ የጸጥታ ሃይል አባላት እና ሌሎች አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሰሞኑንም በህገ-ወጥ መንገድ አስፈራርተው ከግለሰቦች ገንዘብ የተቀበሉ ሶስት የፌደራል ፖሊስ አባላት እና አንድ ሲቪል ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሚኒስቴሩ አመልክቷል ።

ተመሳሳይ ድርጊቶች በፈፀሙ ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል አባላትና ሌሎችም አካላት ላይ የመዛግብት ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያሉት የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ አወል ሱልጣን ኅብረተሰቡ ጥቆማ ማድረሱን መቀጠል አለበት ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሕገ ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:46 0:00


XS
SM
MD
LG