በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎንደር የተፈጸመው ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሌላ የከረመ ቁስል ከፍቷል


በጎንደር የተፈጸመው ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሌላ የከረመ ቁስል ከፍቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

በጎንደር የተፈጸመው ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሌላ የከረመ ቁስል ከፍቷል

ባለፈው ሚያዚያ ወር በሰሜን ኢትዮጵያ በሙስሊሞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት 30 ሰዎች ሞተው 100 የሚሆኑ ከቆሰሉ በኋላ ክስተቱ በክርስቲያኖች ላይ የበቀል ጥቃት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል የላል የቪኦኤው ሄንሪ ዊልኪንስ ከጎንደር በላከው ዘገባ፡

የዓይን ምስክሮችና የማህበረሰብ መሪዎች የግጭቱ መንስሄ ነው ብለው የሚያምኑትን ምክንያት ለቪኦኤው ዘጋቢ ተናግረዋል።

ጎንደር ባለፈው ወር ከተፈጸመውና የበርካቶችን ህይወት ከቀጠፈው ሃይማኖትን መሰረት ካደረገው የቡድን ጥቃት መዘዝ አሁንም ገና አላገገምችም።

የአንድ የእስልምና መሪን የቀብር ሥነ ስርዓት ተከትሎ ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ “በሃይማኖቶች መካከል የሚደረግ ግጭት” ብሎ በጠራውና በጎንደርም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች እጅግ አሳስቦኛል ብሏል።

ሃገሪቱ በተራዘመ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለች በመሆኑ የሃይማኖት ግጭት ከተጨመረበት ባለው ችግር ላይ ሌላ ችግር መጨመር ነው ይላሉ የኣካባቢው የፖለቲካ ተንታኞች።

ጥቃቱ የተፈጸመው በአንድ የቅዳሜ ገበያ ሲሆን አንዳንዶች የሟቾችን ቁጥር ስምንት ሲያደርጉ ሌሎች ደግሞ ሰድሳ ያደርሱታል። አንዳንድ ነዋሪዎች ሟቾቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ ናቸው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ክርስትያኖችም እንዳሉበት ይናገራሉ።

የጎንደሩ ክስተት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የበቀል ጥቃትን ሲያስከትል በመዲናዋ አዲስ አበባ ህንጻዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በጎንደር ያሉ ባለሥልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ሊወጡ የሚችሉ ገለልተኛ ዘገባዎችን በዓይነ ቁራኛ እየተከታተሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ቴሌኮም ደግሞ በጎንደር ከተማ የኢንተርኔት አገልግሎቱን አቋርጧል። ነገር ግን ቪኦኤ የዓይን ምስክሮችን ለማናገር ችሏል። አስናቀው ካሴአንዱ የዓይን ምስክር ናቸው።

“የቀብሩ ሥነ ስርዓት ማጠናቀቂያ ላይ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወጣቶች የቀብሩን ቦታ ለመከለል የሚጠቀሙበትን ድንጋይ በአቅራቢያው ካለው ቤተክርስቲያን ወሰዱ። ያኔነው በሁለቱም ወገን ያሉ ወጣቶች ወደ ግጭት የገቡት። ቀውስ ነበር” ብለዋል ምስክሩ።

ሌሎች የዓይን ምስክሮች ደግሞ ጥቃቱ ሆን ተብሎ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢላማ ያደረገና ለበርካታ ቀናት የተፈጸመ ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠይቋል። ፖሊስ በበኩሉ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አንድ የክርስትና ሃይማኖት መሪ ግን የተባበሩት መንግሥታትን በመውቀስ ክስተቱ የተናጥል ሲሆን በከተማው በሚገኙ የክርስትናና እስልምና ተከታዮች መካከል መልካም ግንኙነት እንዳለ ተናግረዋል።

ግጭቱ የፖለቲካ አጀንዳ ባላቸው ወገኖች እንዲሁም አማጽያን የተፈጸመ ነው ብልዋል ቀሲስ ዮሴፍ ደስታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።

“እኛ እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግጭቱ መነሻውን ሌላ ቦታ ያደረገና ሃይማኖትን እንደ ሽፋን የተጠቀመ ነው ብለን ነው የምናምነው። ውጫዊ ሃይሎች በተለይም የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሃይሎች ከግጭቱ ጀርባ አሉ” ሲሉ ተደምጠዋል ቀሲስ ዮሴፍ።

የጎንደር እስልምና ም/ቤቱ ሞላ ይብሬ በበኩላቸው ግጭቱ ለዓመታት ሲጠመቅ የኖረ ነው ይላሉ።

“ከ2016 ጀምሮ ምልክቶች ነበሩ። እነዚህን ምልክቶች ከለየን በኋላ ለሚመለከታቸው የመንግስት ቢሮዎች ሪፖርት አድርገናል። የማይገባ የሃይማኖት ትምህርት በተለይም አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ይበልጣል የሚለው በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት አንዱ ነው። የሌሎችን ሰብዓዊነት የሚያራክሱ በታክሲዎች ላይ የተሳሉ ስዕሎች ነበሩ” ብለዋል ሞላ ይብሬ።

በጎንደር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወካይ እንዳሉት አንዳንድ ሰባኪዎች አስተምዕሮቱ ከሚፈቅደው ውጪ ባሉ ትርክቶች ላይ ተሰማርተው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነርሱ የቤተክርስትያኗ ወኪሎች አይደሉም ብለዋል።

አንድ የአካባቢው ተንታኝ በበኩላቸው የጎንደሩ ግጭት ምናልባትም ከሃይማኖት እንዲሁም ክክልል ማንንት ጋር ሊገናኝ የችላል ባይ ናቸው። ጎንደር በምትገኝበት የአማራ ክልል የብሄር ማንነት ስሜት በቅርቡ እያደገ መጥቷል ብለዋል ተንታኙ ተርያ ኦስትቦ በፍሎሪዳ ዩኒቨርስቲ የሃይማኖት ትምህርት ክፍል።

ተርያ ኦስትቦ አክለውም፣

“የአማራ ክልልን በተመለከተ ገራሚ ነገር አለ። በጎንደር፣ ጎጃምና ሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች እራሳቸውን እንደ አማራ አይመለከቱም። ተመልክተውም አያውቁም። በዚህ ክልል አማራ ማለት ክርስቲያን በተለይም የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማለት ነው። ስለዚህ እኔ እንደማስበው ይህ በክልሉ ውስብስብ የብሄር ማንነትን ስንመለከት የምናገኘው አስፈላጊ ነጥብ ነው” ብለዋል።

ጥቃቱን በተመለከተ ምርመራው የቀጠለ ሲሆን በጎንደር ያለው ድባብ ግን አሁንም ውጥረት ያለበት ነው።

XS
SM
MD
LG