በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተዋል


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሥራ ጉብኝት በዛሬው እለት ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና በሌሎች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለተፋሰሱ ሀገራትም አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ እና የሱዳን ህዝብም በህዳሴ ግድብ ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በበኩላቸው በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች በቴክኒካል ውይይቶች እንደሚፈቱ እምነታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የመልማት ፍላጎቷን ሱዳን እንደምታከብር እና እንደምትደግፍ አብደላ ሀምዶክ ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ ሁለቱ ሀገራት በሚያዋስናቸው ድንበሮች ላይ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በውይይት ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሷል።

መሪዎቹ በተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮች እና የሁሉቱን ሀገራት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

XS
SM
MD
LG