በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ጦሯን ከትግራይ ክልል ካላስወጣች ማዕቀብ ሊጣል እንደሚችል አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ


ኤርትራ ጦሯን ከትግራይ ክልል ካላስወጣች ማዕቀብ ሊጣል እንደሚችል አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

ኤርትራ ጦሯን ከትግራይ ክልል ካላስወጣች ማዕቀብ ሊጣል እንደሚችል አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በስም ያልጠቀሳቸው ባለሥልጣኑ፣ የኢትዮጵያን የሠላም ሥምምነት በተመለከተ ትናንት በስልክ በሰጡት ማብራሪያ “የናይሮቢው ሥምምነት የኤርትራ ኃይሎች በኢትዮጵያ ስለመኖራቸው እውቅና የሚሰጥ ነው” ብለዋል፡፡

የሥምምነቱን ተፈጻሚነት ከማረጋገጥ አንፃር “አስፈላጊ ከሆነ ማዕቀብ ከመጠቀም ወደ ኋላ አንልም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ለተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሲሰጡ ለሠላም ሥምምነቱ ተፈጻሚነት መንግሥታቸው ቁርጠኛ እንደሆነ መግለጻቸውን ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለሥልጣኑ ተናግረዋል፡፡ ህወሐትም መሰል አቋም ስለመያዙ ገልፀዋል፡፡

በሥምምነቱ መሰረት ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ መግባት መጀመሩንም የገለጹ ሲሆን የዓለም ምግብ ፕሮግራምም ዛሬ ከሰኔ 2013 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በጎንደር በኩል እርዳታ ማስገባቱን አመልክቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG